”እግዚአብሔርን ጠበኩት ፤ አላሳፈረኝም” ሱዜ ሎፔዝ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ሱዜ ሎፔዝ የተባለች እናት ልጅ ለመውለድ ለ20 ዓመታት ያህል ስትጠብቅና ስትጸልይ ከቆየች በኋላ የሕክምና ባለሙያዎች በፍጹም ያልጠበቁትን አስደናቂ እርግዝና አስተናግዳለች።

እስከ ወሊድ ጊዜ ድረስ በማህጸን ጽንስ መቋጠር የማትችልበት ሁኔታ የገጠማት ይህች እናት ፣ የሕክምናውን ዓለም አይሆንም አበቃ ብሏት የነበረ ቢሆንም ይስሀቅ በአብርሃም ቤት እንደገባ ለእርሷም እንዲሁ ሆኖላታል።

​ይህን አጋጣሚ “የእግዚአብሔር ተአምር” ስትል የምትጠራው ሱዜ የልጇ መወለድ የጸሎቷ ምላሽ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያረጋገጠ ትልቅ ሕያው ምስክር እንደሆነ ትናገራለች።

ረጅም ዓመታትን በትዕግሥትና በአምላክ ላይ በመደገፋ ፍሬ ማፍራቱን ያወጀችው ይህች እናት ያገኘችው እያንዳንዱ ነገር ትልቅ ስጦታ መሆኑን በመግለጽ በተስፋ እግዚአብሔርን የሚጠባበቁ ሁሉ አያፍሩም ብላለች።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2