#Ethiopia | በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት በሚገኘው ዊትሊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያስተምሩት ዳሪየስ ዊሊያምስ የተባሉ መምህር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቻቸው መሠረታዊ የሆነ የንባብና የጽሕፈት ችሎታ እንደሌላቸው በመታዘባቸው በለቅሶ የታጀበ ቁጣቸውን ገልጸዋል።
በትምህርት ዘመኑ ላይ የገጠማቸውን ያጋሩት መምህሩ፣ በምሳ እረፍታቸው ወቅት በቀረጹትና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በፍጥነት በተሰራጨው ቪዲዮ ላይ የ17 እና 18 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ተማሪዎቻቸው አራት ቃላትን ብቻ የያዘን ዓረፍተ ነገር አሟልተው መጻፍ አለመቻላቸውን በከፍተኛ በዕንባ ጭምር ተናግረዋል።
መምህር ዳሪየስ እንደገለጹት ለተማሪዎቹ የተሰጠውን የንባብ መልመጃ ደረጃ በደረጃ ያስረዷቸውና አብዛኛውን መልስ በግልጽ አሳይተዋቸው የነበረ ቢሆንም ተማሪዎቹ ሃሳባቸውን በጽሁፍ ማስፈር አልቻሉም።
ተማሪዎቹ ውስብስብ ሃሳቦችን በቃል የመግለጽና የመሞገት ከፍተኛ ብቃት ቢኖራቸውም ያንን ሃሳብ ወደ ጽሁፍ የመቀየር መሠረታዊ ችሎታ ግን እንደጎደላቸው ጠቁመዋል።
ይህ አጋጣሚ በአሜሪካ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ያለውን የጽሑፍና የንባብ ችግር አጉልቶ ያሳየ ነው ተብሏል።
ለቪዲዮው ምላሽ የሰጡ በርካታ አስተያየት ሰጪዎችና የትምህርት ባለሙያዎች ለችግሩ መስፋፋት የተለያዩ ምክንያቶችን ያነሳሉ።
አንዳንዶች የቴክኖሎጂ በተለይም የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መስፋፋት ወጣቶች በራሳቸው የማሰብና የማንበብ ፍላጎታቸውን እንዲያጡ ማድረጉንና ያልበቁ ተማሪዎችን ሳያልፉ እንዲያልፉ የሚያስችሉ የትምህርት ፖሊሲዎችን ተወቃሽ ሲያደርጉ ሌሎች ደግሞ የወላጆች ክትትልና የቤት ውስጥ ድጋፍ ማነስ ለችግሩ ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ይገልጻሉ።
ይህ አጋጣሚ የሕዝብ ትምህርት ቤት መምህራን መሠረታዊ የትምህርት ክህሎት የሌላቸውን ተማሪዎች ለአዋቂነት ሕይወት ለማዘጋጀት የሚገጥማቸውን ከባድ ፈተናና የስነ-ልቦና ጫና የሚያሳይ ነው ተብሏል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.