#Ethiopia | በሳኦ ፓውሎ ክለብ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አውቶቡስ ላይ እፅ ተያዘ።
የክለቡ አባላትና አመራሮች ግን በድርጊቱ እንደሌለበት ተገልጿል።
በብራዚል የፖሊስ አባላት ባደረጉት ፍተሻ 86 ኪሎ ግራም የሚመዝን ማሪዋና በአውቶቡስ ላይ መያዛቸው ነው የተገለፀው።
አውቶቡሱ የሳኦ ፓውሎ እግር ኳስ ክለብ ለተለያዩ ጉዞዎች በኮንትራት የሚጠቀምበት የኪራይ ተሽከርካሪ ነው ተብሏል።
በወቅቱ የክለቡ ተጫዋቾችም ሆኑ የስፖርት ቡድኑ አባላት በተሽከርካሪው ውስጥ አልነበሩም ሲሉ ፖሊሶች ተናግረዋል።
የሳኦ ፓውሎ ክለብም በጉዳዩ ላይ እጁ እንደሌለበትና ከድርጅቱ ጋር ያለውን አገልግሎት በተመለከተ ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#SãoPaulo #Bolivia
#TeamBus #𝐌𝐀𝐑𝐈𝐉𝐔𝐀𝐍𝐀
Source: GetuTemesgen









No comments yet.