ቴዎድሮስ አምዴ 16 ዓመታት የፈጀውን «ምስክር» የተሰኘ የደብል ቤዝ ድራም ኢትዮ-ጃዝ አልበም ሊያስመርቅ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

🎼

#Ethiopia | ​በሀገራችን የድራም ሙዚቃ አጨዋወት ታሪክ ውስጥ ስማቸው በገነነው የሙዚቃ ባለሙያ ቴዎድሮስ አምዴ የተቀናበረውና 11 የኢትዮ-ጃዝ ሙዚቃዎችን የያዘው «ምስክር» የተሰኘ አዲስ አልበም በመጪው አርብ በናሆም ሬከርድስ የYouTube ቻናል በይፋ ለአድማጮች ይበቃል።

​ይህ አልበም ለጥናት፣ ለዝግጅትና ለፈጠራ ሂደቱ በአጠቃላይ 16 ዓመታትን የፈጀ ሲሆን፣ ለሀገራችን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ልዩና አዲስ ኦሪጅናል የጃዝ ሥራ እንደሆነ ተገልጿል።

በአልበሙ ላይ 8 ታዋቂ የቤዝ ጊታር ተጫዋቾችን (አብይ ሰለሞን፣ ሄኖክ ተመስገን፣ ዳግማዊ አሊ እና ሌሎችንም) ጨምሮ በሊድ ጊታር፣ ኪቦርድ፣ ትሮምቦን እና ፍሉት የታወቁ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።

​በተጨማሪም የሙዚቃ ባለሙያው ቴዎድሮስ አምዴ፣ የደብል ቤዝ ድራም አጨዋወትን ያለ አስተማሪ ለመማር የሚያስችል ባለ 218 ገጽ መጽሐፍ አዘጋጅቶ ለአንባቢዎች ያቀረበ ሲሆን፤ መጽሐፉ በአብርሆት ቤተ መጻሕፍትና በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ይገኛል።

​ልዩ መታሰቢያ፡
ይህ አልበም በሥራው ዝግጅት ወቅት አብረው ለሠሩትና አሁን በሕይወት ለሌሉት ታዋቂው የትራምፔት ተጫዋች ሻምበል መኮንን መርሻ እና የቤዝ ጊታር ተጫዋች ፋሬው መንግስቱ መታሰቢያነት የተበረከተ ነው።

​#EthioJazz #TewodrosAmde #MeskirAlbum #NahomRecords #EthiopianMusic #DoubleBassDrum



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: