የቴስላ ሰራተኞች በአመት የሚያገኙት ገቢ ኤሎን መስክ በ4 ሰከንድ ልዩነት ያገኘዋል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia |ኤሎን መስክ በ2025 ከቴስላ የተከፈለው አጠቃላይ ክፍያ ከመደበኛ ሰራተኛው በ2.5 ሚሊዮን እጥፍ ይበልጣል።

ቴስላ በፈረንጆቹ 2025 ለዋና ሥራ አስፈፃሚው ኢሎን መስክ የከፈለው አጠቃላይ ክፍያ ከኩባንያው መደበኛ ሰራተኛ ዓመታዊ ገቢ በ2.5 ሚሊዮን እጥፍ እንደሚበልጥ ተነገረ።

የቴስላ መደበኛ ሰራተኛ በአንድ ሙሉ ዓመት የሚያገኘውን ገቢ ኢሎን መስክ በየ 4 ሰከንዱ ልዩነት ውስጥ ያገኘዋል ነው የተባለው።

የአሜሪካ የሰራተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ባወጣው ሪፖርት መሠረት መስክ በ2025 158.3 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ ጥቅማጥቅም እና የትርፍ ድርሻ ማግኘቱን ገልጿል።

ይህ ክፍያ በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች እና በተራ ሰራተኞች መካከል ያለውን ሰፊ የገቢ ልዩነት በግልጽ የሚያሳይ እንደሆነ ተጠቅሷል።

የሰራተኛ ማህበራት ተወካዮች ይህ ዓይነቱ ከፍተኛ የክፍያ ልዩነት በኢኮኖሚው ላይ ያለውን የገቢ አለመመጣጠን እንደሚያሰፋ በመግለጽ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የቴስላ ባለአክሲዮኖች በበኩላቸው መስክ ለኩባንያው ለሚያበረክተው የፈጠራና የዕድገት አስተዋጽኦ የሚገባው ማበረታቻ ነው በማለት ይከራከራሉ።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Tesla #ElonMusk #CEO #average #worker
#federation #labor #unions


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: