በሸገር ከተማ ንፋስ ስልክ ተብሎ የሚጠራው የጋራ መኖሪያ መንደር የውሃ እጥረት በማጋጠሙ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። “የወደፊቱ ከተማ” በሚል የምትታወቀው ሸገር ከተማ መሰረታዊ የህዝብ አገልግሎት የሆነውን የመጠጥ ውሃ ማቅረብ ተሳናት ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
በአካባቢው ውሃ ከተለቀቀ ሳምንታት መቆጠራቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በየቀኑ ለዕለት ተዕለት ፍጆታ የሚሆን ውሃ ለማግኘት ረጅም ርቀት ለመጓዝ እና ለተጨማሪ ወጪ ለመዳረግ መገደዳቸውን ገልጸዋል።
ሁኔታው በተለይም ህፃናትና አረጋውያን ባሉባቸው ቤተሰቦች ዘንድ የከፋ እንግልት መፍጠሩን ጠቁመው፣ የሚመለከተው የመንግስት አካል በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው በአጽንኦት ጠይቀዋል።
Source: FastMereja








No comments yet.