#Ethiopia | በታሪክ ማህደር ውስጥ አንዳንዶቹ አባባሎች አስቂኝ ይመስላሉ ነገር ግን ከጀርባቸዉ ያለዉ እዉነታ ሲመረመር አስደናቂና አስገራሚ ፍርሃትን ያዘሉ ናቸው።
ከእነዚህ መካከል ደግሞ የኡጋንዳው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኢዲ አሚን ዳዳ የተናገሩት አባባል በቀዳሚነት ይጠቀሳል።
ኢዲ አሚን ሀገሪቱን በብረት እጅ በያዙበት ወቅት ስለ መናገር ነፃነት ተጠይቀው የሰጡት መልስ ዛሬም ድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ይነሳል።
“የመናገር ነፃነትማ አለህ ነገር ግን ከተናገርክ በኋላ ስላለው ነፃነትህ ዋስትና መስጠት አልችልም” የሚለው።
በወቅቱ አባባሉ እንደ ቀልድ ቢወሰድም በስልጣን ዘመናቸው የታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት የፖለቲካ ተቃዎሞ ስደትና ጭቆና ግን የአባባሉን እውነተኛና አስፈሪ ገጽታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነበር።
አባባሉ በአንድ በኩል ለዛ ያለውና አዝናኝ ቢመስልም በሌላ በኩል ግን ስልጣን ላይ ያሉ አካላት ለነፃ ሀሳብ ያላቸውን አመለካከት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።
በዚህ ዘመንም ስለ ሀሳብ ነፃነት ስለ መናገር መብትና ስለ ዲሞክራሲ በሚደረጉ ውይይቶች ውስጥ ይህ የኡጋንዳው መሪ አባባል እንደ ትልቅ ታሪካዊ ማስታወሻ ይወሰዳል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Uganda #president
#Press #freedom
#speech #IdiAmin
Source: GetuTemesgen









No comments yet.