ናታን ኪርሽ በአፍሪካ የ20 ቢሊዮን ዶላር የሀብት ጣሪያ የደረሱ ሦስተኛው ሰው ሆኑ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአፍሪካ የሀብታሞች የስም ዝርዝር ሰንጠረዥ ላይ አስገራሚና አዲስ ታሪክ ተመዝግቧል።

የስዋዚላንዱ ቢሊየነር ናታን ኪርሽ የሀብት መጠናቸውን የሀብት መጠናቸውን በማሳደግ የ20 ቢሊዮን ዶላር ባለቤት መሆናቸው ተረጋገጠ።

በዚህም መሰረት ናታን ኪርሽ ከናይጄሪያው አሊኮ ዳንጎቴ እና ከደቡብ አፍሪካው ዮሃን ሩፐርት በመቀጠል በአፍሪካ የ20 ቢሊዮን ዶላር የሀብት ጣሪያን የተቀላቀሉ ሶስተኛው ሰው መሆን ችለዋል።

ናታን ኪርሽ የሀብታቸው መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያድግ ያደረገው የአሜሪካ የምግብ ማከፋፈያ ኩባንያቸውን በ29 ቢሊዮን ዶላር ለመሸጥ ያደረጉት ስምምነት ነው ተብሏል።

በ1976 የጀመሩት የምግብ ማቀነባበርያ ኩባኒያቸው ዛሬ በአሜሪካ 35 ግዛቶች 166 ቅርንጫፎች ያሉትና በዓመት 16 ቢሊዮን ዶላር የሚያንቀሳቅስ ግዙፍ ተቋም ነው።

አሊኮ ዳንጎቴ የሀብታሞች ሰንጠረዠ ቀዳሚውን ስፍራ በአስተማማኝ ሁኔታ ይዘዋል።

ደቡብ አፍሪካዊ ቢሊየነር ዮሀን ሩፐርት 20 ቢሊዮን ዶላር የተሻገሩ ሁለተኛ ሰው ናቸው።

አሁን ናታን ኪርሽ 20 ቢሊዮን ዶላር የሀብት መጠን የደረሱ ሶስተኛው ቢሊየነር ሆነዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#africa #billionaire #NathanKirsh #Swaziland #Dangote #Nigeria


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2