አሁን ላይ በቀን ሦስቴ መመገብ ቅንጦት ሆኗል፦የአለም የምግብ ፕሮግራም

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የዓለም የምግብ ፕሮግራም ባወጣው አዲስ ሪፖርት በአለም አቀፍ ደረጃ ዜጎች በምግብ እጦት ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ገልጿል።

ሀገራት ለምግብ የሚያደርጉት እርዳታ በመቀነሳቸው ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የዓለም ዜጎች የረሃብ አለንጋ እየገረፋቸው ይገኛል ሲል ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

እንደ ድርጅቱ መረጃ ከሆነ በአሁኑ ሰዓት በመላው ዓለም ከ700 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ አቅርቦት ይሻሉ።

ከዚህ ቁጥር ውስጥ ከ300 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት አጣዳፊ የምግብ እርዳታ ካልተደረገላቸው ነገ አንመለከታቸውም ሲል ገልጿል።

ለጋሽ ሀገራት እና አለም አቀፍ ተቋማት የሚያደርጉት የገንዘብ እና የቁሳቁስ እርዳታ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ችግሩን የበለጠ አሳሳቢ አድርጎታል።

ይህ የእርዳታ ማነስ እና መቋረጥ በብዙ ሀገራት የሚኖሩ አቅመ ደካሞች እናቶች እና ህፃናት ለህልፈት እየዳረጋቸው ነው ሲል አስጠንቅቋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#starvation #food #program
#War #climate #donations
#poverty #children #women


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2