#Ethiopia | በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ100 በላይ ጋዜጠኞች በስራቸው ምክንያት ህይወታቸውን ያጣሉ ተብሏል።
የመረጃ ነጻነትና የጋዜጠኞችን ደህንነት የሚከታተሉ አለም አቀፍ ተቋማት ባወጡት አዲስ ሪፖርት በየዓመቱ በአለም ዙሪያ በርካታ ጋዜጠኞች እውነትን በመፈለግና ህዝብን በማሳወቅ ሂደት ውስጥ ህይወታቸውን እንደሚያጡ አስታወቁ።
እንደ አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (CPJ) መረጃ ከሆነ በየዓመቱ በላይ ጋዜጠኞችና የሚዲያ ባለሙያዎች ይገደላሉ ብሏል።
ባለፉት 20 አመታት ውስጥ ከ1,600 በላይ ጋዜጠኞች እንደተገደሉም ነው የገለጸው።
በግጭት ቀጠናዎች በታጣቂዎች ጥቃት እንዲሁም በተቃወሟቸው አካላት በሚሰነዘርባቸው ጥቃት ምክንያት ህይወታቸው እንደሚያልፍ ነው የገለፀው።
በጦርነት ቀጠናዎች በሚደረጉ ግጭቶች ሙስናንና ወንጀልን በማጋለጣቸው እንዲሁም በተለያዩ የፖለቲካ አለመረጋጋቶች ምክንያት ጋዜጠኞች ለከፍተኛ አደጋ ይጋለጣሉ ብለዋል።
አለም አቀፍ ድርጅቶችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች መንግስታትና የተለያዩ አካላት ለጋዜጠኞች አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
በተጨማሪም በጋዜጠኞች ላይ ጥቃት የሚያደርሱ አካላትን ለፍርድ እንዲያቀርቡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#CPJ #journalist #crimes #information #warzone
Source: GetuTemesgen









No comments yet.