በጫካ ተሸፍኖ ለ20 ዓመታት ያህል የተረሳው አየር ማረፍያ ተገኘ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በፓራጓይ ለ20 ዓመታት የጠፋው አውሮፕላን ማረፊያው በመጨረሻም የዶሮ ማርብያ ሆኖ መገኘቱ ኦዲቲ ሴንትራል ፅፏል።

በላቲን አሜሪካዊቷ ሀገር ፓራጓይ የሚገኘውና አየሮድሮም ደ ሳን ፔድሮ በመባል የሚታወቀው ይህ አነስተኛ የአውሮፕላን ማረፊያ በዛፎች እና በጫካ ተሸፍኖ ስለነበር ለ20 ዓመታት ያህል ከአይን ተሰውሮ ቆይቷል።

ይህ አየር ማረፊያ በይፋ አገልግሎት መስጠት የጀመረው በፈረንጆቹ በ1980ቹ አካባቢ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በወቅቱ አየር ማረፍያው በዋናነት ለአካባቢው የግብርና ምርቶች ማጓጓዣ ለአነስተኛ የግል አውሮፕላኖች እና ለአደጋ ጊዜ የህክምና እርዳታ በረራዎች አገልግሎት ይሰጥ ነበር ተብሏል።

በፈረንጆቹ 2000 አመት አካባቢ የአካባቢው የመሰረተ ልማት በመስፋፋቱ እና አየር ማረፊያው በቂ የፋይናንስ ድጋፍ በማጣቱ ምክንያት ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ ለ20 አመት ቆይቷል።

ከ20 አመታት ፍለጋ በኋላ በቅርቡ በሳተላይት ምስል አማካኝነት እንደገና መገኘቱ ተሰምቷል።

የሚገርመው ነገር በውስጡ ይኖሩ የነበሩ የአካባቢው ሰዎች አየር ማረፊያውን ለዶሮ እርባታ አገልግሎት ሲጠቀሙበት ነበረ ተብሏል።

የሀገሪቱ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣናት በሳተላይት ምስሉ አማካኝነት ቦታውን እንደገና ካወቁ በኋላ አየር ማረፊያውን መልሶ ጥገና በማድረግ ወደቀድሞ አገልግሎቱ ይመለሳል ብለዋል ሲል የጻፈው ኦዲቲ ሴንትራል ነው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Paraguay #Airport
#Audditycentral #oddnews
#Technology #industry


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2