ቡርኪና ፋሶ ለጋዜጠኞች ወታደራዊ ስልጠና መስጠት ጀመረች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መንግስት ለጋዜጠኞች ወታደራዊ ይዘት ያለው “የሀገር ፍቅር” ስልጠና መስጠት መጀመሩ ተገለጸ።

በኡጋዱጉ አቅራቢያ በተካሄደው በዚህ ስልጠና የመጀመሪያውን ዙር ያጠናቀቁት 44 ጋዜጠኞች የወታደር ዩኒፎርም በመልበስ እና ጠመንጃ በመያዝ የስድስት ቀናት የሰራዊት ልምምድ አድርገዋል።

​መንግስት ሀገሪቱ በታጣቂዎች እያጋጠማት ያለውን የሽብር ጥቃት ለመመከት የዜጎችን የሀገር ፍቅር ስሜት ማጎልበት አስፈላጊ ነው ብሎ በማመኑ ይህን እንዳደረገ ቢገልጽም የፕሬስ ነፃነት ተሟጋቾች ግን አሰራሩ የጋዜጠኞችን ገለልተኝነት እና ሙያዊ ነፃነት ያሳሳል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ይህ የሀገር ፍቅር ማነቃቅያ ስልጠና ከጋዜጠኞች በተጨማሪ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችም መሰጠት መጀመሩ ታውቋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2