ታሪካዊቷ ደባርቅ

- Advertisement -
Sidebar AD

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መገኛ የሆነችውን ታሪካዊቷ ደባርቅን በጋራ እናልማ!

በ1674 ዓ.ም. በአዲያም ሰገድ እያሱ ዘመነ መንግሥት በደጃች አምሳሌ ዘሴ የተቆረቆረችው ታሪካዊቷ ደባርቅ፣ የዘመናትን ታሪክ አስተምራ ዛሬም በአዲስ የልማት ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መግቢያና የቱሪዝም ማዕከል የሆነችው ደባርቅ፣ ከገናና ታሪኳና ከሚያስደምሙ የተፈጥሮ ሀብቶቿ ጋር የሚመጥን ዘመናዊ የከተማ ገጽታ ለመላበስ ዝግጅቷን አጠናቃለች።

ይህንን ታላቅ የልማት ራዕይ እውን ለማድረግም በመጪው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ትልቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ ተዘጋጅቷል።

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የምትኖሩ የደባርቅ ተወላጆች፣ ባለሀብቶች፣ ባለሙያዎችና የከተማዋ ወዳጆች በሙሉ፤ ይህ የልማት ጉዞ የእያንዳንዳችንን አሻራ ይፈልጋል።

ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም.
ሂልተን ሆቴል — አዲስ አበባ
በዚህ ታላቅ መድረክ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ ዲፕሎማቶች፣ ባለሀብቶችና ታላላቅ የኪነ ጥበብ ሰዎች ይገኛሉ።

የደባርቅን ታሪካዊ ክብር የሚመጥን ከተማ ለመገንባት በገንዘብዎ፣ በዕውቀትዎ፣ በሙያዎና በቁሳቁስ ድጋፍዎ የዚህ ታሪካዊ ለውጥ አካል ይሁኑ!

በተጨማሪም ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም.በአዲስ አበባ ጃንሜዳ ደባርቅን በማልማት ላይ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ባለሀብቶች ልዩ የኢንቨስትመንት ዕድል ተዘጋጅቷል።

የከተማዋ አስተዳደርም ወደ ደባርቅ ለሚመጡ ባለሀብቶች ሙሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ሲሆን፣ ለኢንቨስትመንት የሚውል የለማ መሬትም አዘጋጅቷል።

🔹 ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ — 21.5 ሄክታር
🔹 ለአገልግሎት፣ ለቱሪዝምና ለሆቴል ዘርፍ — 20 ሄክታር
እነዚህ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለሚመጡ ባለሀብቶች የሚያበረታቱ ዕድሎችን ይፈጥራሉ።

ደባርቅን ማልማት ታሪክን ማደስ ነው!
ደባርቅ የትናንት ታሪክ ብቻ ሳትሆን፣ የነገ ትውልድ ተስፋ ነች።

ከተማዋን ማልማት፣ ታሪኳን ማደስ፣ ቱሪዝሟን ማሳደግ፣ ኢንቨስትመንትን መሳብ እና ለትውልድ የሚተላለፍ ዘላቂ ልማት መፍጠር ነው።

ደባርቅን በጋራ እናልማ! ታሪክን እንጠብቅ፣ ዛሬን እንገንባ፣ ነገን እናዘጋጅ!






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2