#Ethiopia | በማላዊ እየተካሔደ በሚገኘው ቀጠናዊ የፓርላማ አባላት ጉባኤ ላይ የናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ህግ አውጪዎች በስደተኞች ጉዳይ ግጭት ውስጥ ገቡ።
በአህጉራዊ ጉባኤው ላይ በደቡብ አፍሪካ እና ናይጄሪያ ህግ አውጪዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በደ ግጭት በማምራቱ ምክንያት ጉባኤው ሳይጠናቀቅ ተበትኗል።
ይህ ከፍተኛ የሀሳብ መፋጨት የስብሰባውን አዳራሽ በጩኸትና በተቃውሞ እንዲናጥ አድርጎት እንደነበረ ነው የተገለፀው።
የስደተኞች ጉዳይ ከደቡብ አፍሪካ በመሪዎችና በሌሎች ጎረቤት ሀገራት መስፋፋቱ ቀጠናዊ ውጥረቱን የበለጠ እንዲወሳሰብ አድርጎታል ተብሏል።
ይህ ያልተጠበቀ ክስተት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ፍጥጫ እንዲያይል አድርጎታል።
በዴሞክራሲ ሰብአዊ መብቶች እና ቀጣናዊ ትብብር ላይ ለመምከር ከ300 በላይ የፓርላማ አባላትና ባለስልጣናት በማላዊ እየመከሩ ይገኛል።
በዚህ ስብሰባ ላይ የተፈጠረው አለመግባባት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት የበለጠ አሻክሮታል።
የአፍሪካ ህብረት እና የቀጠናው መሪዎች በጉዳዩ ላይ በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገቡ ጥሪዎች እየቀረቡ ይገኛል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Southafrica #Nigeria #Malawi #AfricaUnion #diplomacy
Source: GetuTemesgen









No comments yet.