#Ethiopia |
ሀገራቸው ህንድ የ2036ቱን የኦሊምፒክ ውድድር ለማስተናገድ ካላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ጎን ለጎን በውድድሩ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ ያለመ አገር አቀፍ የታላላቅ ስፖርተኞች ፍለጋ ፕሮግራም እንደሚጀምር የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቱን 80ኛውን የነፃነት ቀን ምክንያት በማድረግ ከቀይ ምሽግ ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር ከ5 እስከ 15 ዓመት የሆናቸውን ታዳጊዎች በመመልመል ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስፖርተኞችን ለማፍራት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የቀደሙት የስፖርት ድጋፍ ፕሮግራሞች ውጤታማ መሆናቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ፣ ህንድ በስፖርቱ ዓለም የራሷን ቦታ እየያዘች መሆኗንና በ2030 የሚካሄደውን የኮመንዌልዝ ጨዋታዎችን እንደምታስተናግድ አብራርተዋል።
በኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ የሀገሪቱን ተሳትፎ ወደ ሶስት አራተኛ ከፍ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን ለዚህም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ጨምሮ የተለያዩ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን በመጠቀም የታዳጊዎችን የስፖርት ብቃት የመለየት ስራ ይከናወናል።
በተጨማሪም ሀገሪቱ በቅርብ ወራት ውስጥ በርካታ ዓለም አቀፍ የስፖርት ኩነቶችን ለማስተናገድ ዝግጅት ማድረጓን ተናግረዋል።
በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ 80ኛውን የነፃነት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።
#india #independenceday #harghartiranga #narendramodi #news #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa




Source: GetuTemesgen








No comments yet.