ሆርሙዝ የአሜሪካ የግዛት አካል አድርጌ በቅርቡ አውጃለሁ! ~ ትራምፕ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | አሜሪካ በቅርቡ ለዓለም የነዳጅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ እና የማዳበሪያ አቅርቦት ወሳኝ የሆነውን የሆርሙዝ የባሕር መስመር የግዛቷ አካል እንደምታደርግ ገልጸዋል።

አሁን ላይ ከፍተኛ ሽንፈት እየገጠማት ያለችውን ኢራንን ድል አድርገን ከጨረስን በኋላ፣ በቅርቡ የሆርሙዝ ወሽመጥን የአሜሪካ ግዛት አድርጌ አውጃለሁ ሲሉ ትራምፕ በኒው ዮርክ ግዛት ጋርደን ሲቲ በሚገኝ የፖሊስ አካዳሚ በተደረገ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

ይህ እውነት ነው” ሲሉም አክለዋል።

የፕሬዚዳንቱ ንግግር ከአምስት ወር በላይ በቆየው የኢራን ጦርነት ላይ ዋሺንግተን የፖሊሲ ለውጥ ስለማካሄዷ ወይም ታስቦበት የተሰነዘረ አስተያየት ስለመሆኑ ምንም የታወቀ ነገር የለም።

የኢራን ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካዜም ጋሪባባዲ የትራምፕን አስተያየት ከሰሙ በኋላ ወሽመጡ በኢራን ቁጥጥር እና ሥልጣን ሥር ይቆያል “ምንም አንረበሽም” በማለት ተናግረዋል።

አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት 21 2018 ዓ.ም. በጋራ በመሆን ኢራን ላይ ጦርነት ካወጁ ወዲህ የሆርሙዝ ወሽመጥ በቋሚነት ተዘግቷል።

አሜሪካ እና ሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የኢራን ጦር በጀመረበት ወቅት የአገሪቱን የኒውክሌር ፕሮግራም ማስቆም ዋነኛ ዓላማቸው መሆኑን ሲናገሩ ነበር።

ኢራን በበኩሏ ለሚፈጸምባት ድብደባ በባሕረ ሰላጤው አገራት የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠፈሮችን እንዲሁም በወሽመጡ በኩል የሚያልፉ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን በማጥቃት ምላሽ ሰጥታለች።

አሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች የሚገቡ እና የሚወጡ መርከቦችን እንቅስቃሴ የገደበች ሲሆን የሁለቱ አገራት መካረር የዓለም ነዳጅ ዋጋ ቅናሽ እንዳያሳይ አድርጎታል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Hormuz #USA #president #Trump #political #war


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2