#Ethiopia | የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ለገንዘብ ህትመት ብቻ በየአመቱ ከ350 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ እንደሚያደርጉ ተገለፀ።
የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የገንዘብ ዝውውራቸውን ለማስቀጠል አዳዲስ የብር ኖቶችን ለማስገባት እና ያረጁትን ለመተካት በየአመቱ ከ350 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ለህትመት አገልግሎት ብቻ ወጪ እንደሚያደርጉ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
ይህ ከፍተኛ የፋይናንስ ወጪ የሚወጣው አብዛኞቹ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት በራሳቸው ሀገር ውስጥ ዘመናዊ የገንዘብ ማተሚያ ተቋማት ስለሌሏቸውና የህትመት አገልግሎቱን ከአውሮፓ ኩባንያዎች በመግዛታቸው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።
በቀጠናው ከሚገኙ ሀገራት መካከል ስምንቱ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት (ቤኒን፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ኮትዲቯር፣ ጊኒ-ቢሳው፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ሴኔጋል እና ቶጎ) የሚጠቀሙትን የጋራ ገንዘብ ዛሬም ድረስ የሚያሳትሙት በፈረንሳይ እንደሆነ ተጠቅሷል።
ባለሙያዎች እንደሚመክሩት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ይህንን ከፍተኛ ወጪ ለመቀነስ የዲጂታል ክፍያ ስርዓቶችን ማስፋፋት ወይም በጋራ የሀገር ውስጥ የህትመት ማዕከላትን መገንባት አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው ብለዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#France #moneyprinting
#WestAfrica #economy
Source: GetuTemesgen








No comments yet.