የትግራይ ክልል አዲስ ስርዓተ ትምህርት ይፋ አደረገ፤ የአማርኛ ቋንቋ አሰጣጥ ላይ ለውጥ ተደረገ❗❗
የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ላለፉት 16 ዓመታት ሲሠራበት የነበረውን ስርዓተ ትምህርት በመቀየር፣ በ14 የዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ባለሙያዎች የተዘጋጀ አዲስ ካሪኩለም ማዘጋጀቱን ገለጸ። ቢሮው እንዳስታወቀው የቀድሞው ስርዓተ ትምህርት የክልሉን ራዕይ ለማሳካትና ትምህርቱን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና ከዘመኑ የቴክኖሎጂ እድገት ጋር ለማጣጣም በቂ ባለመሆኑ አዲሱ ካሪኩለም በ2019 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሂደት ላይ በሥራ ላይ ይውላል ተብሏል።
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት ትልቅ ትኩረት ከተሰጣቸው ነጥቦች መካከል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት አንዱ ሲሆን፣ ከአሁን ቀደም ከሦስተኛ ክፍል ይጀምር የነበረው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት አሰጣጥ ወደ ሰባተኛ ክፍል እንዲዘገይ ተደርጓል። በተጨማሪም በቀድሞው ካሪኩለም ያልነበረው የግብረ-ገብ ትምህርት በአዲሱ መዋቅር ውስጥ የተካተተ ሲሆን፣ ለዝግጅቱም የእስያ የስነ-ምግባር እንዲሁም የሰሜንና ምዕራብ አውሮፓ የእኩልነትና ተጠያቂነት ተሞክሮዎች ጥቅም ላይ ውለዋል።
ለዚሁ ስርዓተ ትምህርት ማዘጋጃ የሚሆን $550,000 ዶላር በዩኒሴፍ የተፈቀደ ቢሆንም፣ በፌዴራል መንግሥት በኩል በጀቱ ሙሉ በሙሉ ባለመልቀቁ ምክንያት እስካሁን ለስራ የዋለው $200,000 ዶላር ብቻ መሆኑን የትምህርት ቢሮው መረጃ ያመላክታል።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.