#Ethiopia | ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ የቴአትር ጥበብ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት ታላቁ አርቲስት ደበበ እሸቱ (ጋሽ ደቤ) ህልፈት አንደኛ ዓመት መታሰቢያ በአዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተካሂዷል።
ይህ ዝክረ መርሃ ግብር ታላቁ አርቲስት በሕይወት ዘመናቸው ለሀገር፣ ለሕዝብና ለኪነ-ጥበብ ያበረከቱትን የላቀ አሻራ ለማስታወስ የተዘጋጀ ነው።
አርቲስት ደበበ እሸቱ የጥበብ መሠረታቸውን በጣሉበት ተፈሪ መኮንን ኮሌጅ ስምና ዝና ከፍ እንዲል በከፍተኛ ትጋት የሠሩ ሲሆን፣ ተቋሙ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ለሀገር የሚበጁ ባለሙያዎችን እንዲያፈራ ያደረጉት ጥረት በታሪክ የሚዘከር መሆኑ ተመላክቷል።
በተለያዩ ሀገራት በመዘዋወር ያገኟቸውን የቴአትር ዕውቀቶች ለወጣቶች በማጋራት ዘርፉ ተገቢውን ስፍራ እንዲይዝ የጎላ ሚና ተጫውተዋል።
በዕለቱ የተገኙ የሙያው ባለሙያዎች፣ የቀድሞ ተማሪዎችና የቤተሰብ አባላት አርቲስቱ በጥበብ ሙያቸው የከፈሉትን መስዋዕትነት በክብር አውስተዋል።
ከጥበብ ፍቅራቸው ጎን ለጎን እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር የቦርድ አባል በመሆን ያገለገሉት ጋሽ ደቤ፣ ይህ የበጎ አርአያነት አሻራቸው ለቀጣዩ ትውልድ ትልቅ መነሳሳትን የሚፈጥር እንደሆነ ተገልጿል።
#DebebeEshetu #GashDebe #EthiopianTheatre #TeferiMekonnen #EthiopianArtists #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Source: GetuTemesgen









No comments yet.