የኢንሹራንስ ሽፋን ያገኛል ወይ?

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ትላንት ቅዳሜ ነሐሴ 9/2018 ዓ.ም ከቦሌ ቡልቡላ ወደ ኮዬ ፈጪ በሚወስደዉ መንገድ ላይ BYD የኤሌክትሪክ መኪና ከፖል ጋር ተጋጭቶ እሳት በመነሳቱ መኪናዉ ሙሉ ለሙሉ ወደመ ኢንሹራንስ ሽፋን ያገኛል ወይ?

”ስንቶች በምንነዳዉ መኪና ዉስጥ የእሳት ማጥፊያ(Fire Extinguisher) ይዘን እንጓዛለን? ኢንሹራንስ ኩባንኛዋችስ ደንበኛ ዉል ሲገዛ እንዲይዝ ታስገድዳላችሁ?”

አዎ፣ በአጠቃላይ የሙሉ የመኪና ኢንሹራንስ (Comprehensive Motor Insurance) ሽፋን ካለው፣ BYD ኤሌክትሪክ መኪናው በፖል ተጋጭቶ በአደጋው ምክንያት እሳት ተነስቶ ሙሉ በሙሉ ከወደመ፣ የኢንሹራንስ ካሳ ሊያገኝ ይችላል።

ዋናው ነገር ግን የፖሊሲው የሽፋን ውሎች ናቸው።

📌በዚህ ሁኔታ ምን ይመረመራል?

📍Collision/Accidental Damage:- ከፖል ጋር መጋጨቱ በፖሊሲው የተሸፈነ አደጋ ከሆነ፣ የመጀመሪያው ጉዳት ይሸፈናል።

📍Fire Damage:-ከግጭቱ በኋላ የተነሳው እሳት የአደጋው ተከታይ ውጤት መሆኑ ከተረጋገጠ፣ የእሳት ጉዳቱም በሽፋኑ ውስጥ ሊገባ ይችላል።

📍Total Loss :-መኪናው በተግባር ሊጠገን የማይችል ወይም የመጠገኛ ወጪው ከተወሰነው የጠቅላላ ዋጋ መጠን በላይ ከሆነ፣ ኢንሹራንሱ Total Loss ብሎ ሊያስቀምጠው ይችላል።

📍EV Battery:-ይህ በBYD ላይ በተለይ ጠቃሚ ነው። የBattery Pack ጉዳት በፖሊሲው የተሸፈነ መሆኑና ምን ያህል እንደሚሸፈን በተለይ መመርመር ያስፈልጋል።

📌ዋናው ጥያቄ ምንድነው?

📍ግጭቱ በፖሊሲው የተሸፈነ አደጋ ነው?
📍ከግጭቱ በኋላ የተነሳው እሳት ከአደጋው ተከታይ ውጤት ነው?
📍መኪናው Total Loss መሆኑ በግምገማ ተረጋግጧል?
📍የEV Battery እና የBattery-related damage በፖሊሲው ምን ያህል ተሸፍኗል?
📍 የፖሊሲው የማይሸፍናቸው ሁኔታዎች አሉ?

📌ግን ሁለት ነገሮችን መለየት አለብን

Comprehensive Insurance ከሆነ:
👉 ካሳ የማግኘት እድሉ ከፍተኛ ነው፣ የግጭቱና የእሳቱ መንስኤ በምርመራ ከተረጋገጠ።

ሶስተኛ ወገን ብቻ ያለው (Third-Party Only) ከሆነ:
👉 የመኪናውን ራሱን የግጭትና የእሳት ጉዳት በአጠቃላይ አይሸፍንም፤ ዋናው ሽፋን በሶስተኛ ወገን ላይ ለደረሰ ጉዳት ነው።

ስለዚህ BYD በፖል ተጋጭቶ ፣እሳት ተነሳ ፣ሙሉ በሙሉ ወደመ በሚለው ሁኔታ፣ Comprehensive policy ካለው የካሳ ጥያቄው በጣም ጠንካራ ነው። ነገር ግን የመጨረሻ ውሳኔ በፖሊሲው ውል፣ በአደጋው ምርመራ እና በጉዳቱ ግምገማ ላይ ይመሰረታል::

📍📍📍ለኤሌክትሪክ መኪና ባለቤቶች:-
EV ሲገዙ የመኪናውን ዋጋ ብቻ ሳይሆን፣ Battery, Fire, Collision, Total Loss እና EV-specific exclusions በፖሊሲው ውስጥ በግልጽ መካተታቸውን ያረጋግጡ።

‘’ኢንሹራንስ ማለት ፖሊሲ መግዛት ብቻ አይደለም፤ ምን እንደተሸፈነ ማወቅም ነው።’’

ሰሎሞን ኦሊ
የኢንሹራንስና ሪስክ ማነጅመንት አማካሪና ባለሙያ

#Insurance #MotorInsurance #EVInsurance #ElectricVehicle #BYD #Claims #TotalLoss #EthiopianInsurance #InsuranceAwareness #DigitalInsurance




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2