ጋዜጠኛ ሳምሶን አንተነህ እባላለሁ በOBN የአማረኛ መዝናኛ ፕሮግራሞች አዘጋጅና አቅራቢ ነኝ። የማለፊያ እንግዳና መጽሔት ሾው የማያዘጋጃቸው ፕሮግራሞች ናቸው።
ከዚህ ቀደም ለመጀመሪያ ግዜ በተዘጋጀው የ”African media Award” በ “Outstanding Afrocentric Entertainment Program” 📺 እጩ እንደነበርኩ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው። አሁን ደግሞ አውስትራሊያ በሚዘጋጀው የFOA (Focus on Ability Film Festival) በ International Documentary Film ዘርፍ በ”The Complete Person”እጩ ነኝ።
The Complete Person በምን ላይ ያተኮረ ነው?
Focus on Ability Film Festival ብርቱና ታታሪ የሆኑ የአካል ጉዳተኞችን ታሪክ መነሻ በማድረግ የይቻላል መንፈስ ማጎናጸፍ ዋነኛ ትኩረቱ ነው። ይህንን ከግምት በማስገባት The Complete Person የተሰኘ ሚኒ ዶክመንተሪ ለዓመታት በፀጉር ማስተካከል ላይ ተሰማርቶ በሚሰራ “ደና ያቤሎ” በተባለ ግለሰብ ህይወት ላይ የሚያጠነጥን ታሪክ ነው። ደና ያቤሎ በፖሊዮ ምክንያት ለአካል ጉዳተኝነት ቢጋለጥም ልመናን ተፀይፎ በሙያው ቤተሰቡን የሚያስተዳድር በመሆኑ The Complete Person (ሙሉ ሰው) የሚል ርዕስ ተሰጥቶት በጋዜጠኛ ሳምሶን አንተነህ ተፅፎና ተወጋጅቶ ቀርቧል። የሚከተለውን Link በመጫን ድምፅ ትሰጡኝ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ።
በድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ስምና Email ከሞሉ በኃላ የማረጋገጫ (Confermation code) በEmail የሚላክ በመሆኑ የሚላከውን Code በአግባቡ ይምሉ።
https://beta.focusonability.com.au/films/2026/the-complete-person-12046

Source: FastMereja









No comments yet.