አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአራት አፍሪካ ሀገራት ከባድ ውሳኔ አሳለፈች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ካሜሩን እና ኢትዮጵያ ዜጎች ተሰጥቶ የነበረውን ጊዜያዊ መኖሪያ ፈቃድ ማቋረጡን ተገልጿል።

ይህ ውሳኔ በአገራቸው ባለው የፀጥታ፣ የጦርነት ወይም የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት በአሜሪካ ህጋዊ የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ አግኝተው የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ህጋዊ ከለላ የሚነጥቅ ነው።

ህጉ ከአሜሪካ እንዳይባረሩና ህጋዊ የሥራ ፈቃድ እንዲያገኙ የሚያስችል የሰብዓዊ መብት ከለላ ፕሮግራም ነው።

የትራምፕ አስተዳደር ፕሮግራሙ ስሙ እንደሚገልጸው “ጊዜያዊ” መሆን አለበት በሚል እና በነዚህ አገራት ያሉ ሁኔታዎች አሁን ላይ ዜጎቻቸው እንዲመለሱ ያስችላሉ በሚል ምክንያት አቋርጦታል።

በካሜሩን እና ደቡብ ሱዳን ላይ የተላለፉት የውሳኔ እርምጃዎች ተግባራዊ የሆኑ ሲሆን በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ላይ የተላለፉት ውሳኔዎች ግን በፌደራል ፍርድ ቤቶች ህጋዊ ሙግት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#USA #temporary #Ethiopia #cameron #Somalia #Sudan


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1