በመካንነት የነበሩት ወላጆቿ ኢያቄምና ሐና በንጽህና በቅድስና ቢኖሩም በወቅቱ የነበሩት ካሕናተ ኦሪት ልጅ ስላልወለዱ መስዋዕታቸውን እንኳን ሊቀበሏቸው ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡
ወላጆቿ ወደ እግዚአብሔር ጸልየው፣ ልጅ ከሰጣቸው ለቤተ እግዚአብሔር ሊሰጡ ስዕለት ገብተው ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለዱ፡፡ እመቤታችን ገና በቅድስት ሐና ማሕጸን ከነበረችበት ወቅት ጀምሮ ተአምራት ታደርግ ነበር፡፡ ቤርሳቤህ የተባለች ሴት የሀናን መጸነስ ስትሰማ በደስታ ልትጎበኛት መጣች፡፡ አንድ አይኗን አጥታ የነበረችው ይህች ሴት ቅድስት ሐናን እንኳን ደስ አለሽ ብላ ሆዷን ከዳሰሰቻት በኋላ በዚያው እጇ ዓይኗን ብትነካው ዐይኗ በርቶላታል፡፡ ይህን ምሳሌ አደርገው ድውያን እየመጡ ሆዷን ዳሰው ይፈወሱ ነበር፡፡
በቅድስት ድንግል ማርያም መወለድ ወላጆቿ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሀና ፍሬ አጊኝተዋል፡፡ ዓለም ደግሞ የመድኃኒቱን እናት አጊኝቷል፡፡ይህችን ብርሃን፣ የብርሃን እናት ገዳማውያን አባቶችና እናቶች ዘወትር በጸሎታቸው ያስቧታል፡፡“እምነት ያለው ሥራ ይኑረው” እንዲል ቃሉ፣ እኛም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋዋ ከሞትና መቃብር መለየትና ማረግን የሚያመለክተውን ጾመ ፍልሰታን ስንጾም ጾማችንን ከምጽዋት ጋር የታጀበ እናድርገው፡፡
“ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም” በከባድ ንፋስና ዝናብ ምክንያት ቤተ መቅደሱ ፈርሶ ይገኛል፣ መነኮሳቱም በድርቅና በርሃብ ከባድ ፈተና ውስጥ ናቸው።መሬቱ ደርቋል፣ ከጸሎት መልስ የሚቀመስ እህል ጠፍቷል፣ መነኮሳቱ በረሃብና በችግር እየተፈተኑ የዕለት ሕይወታቸውን ለመግፋት በእጅጉ ተቸግረዋል። በመሆኑም በዚህ ቅዱስ ወቅት የጾማችን ፍሬ በምጽዋትና በፍቅር ሥራ ሊገለጥ ይገባል።ለቤተ መቅደሱ መልሶ መገንባት፣ ለመነኮሳቱ ምግብና መሠረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት በአቅማችን እንረባረብ። ለእኛም የእግዚአብሔር በረከትና የእመቤታችን ምልጃ ምክንያት ይሆንልናል።
ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡- 1000766349227
አቢሲንያ ባንክ ፡- 262281132
ለበለጠ መረጃ:- 0944672222 ወይም 0916106921
Source: FastMereja








No comments yet.