ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በዝቅተኛ ወጪ ደስተኛ
መሆን ከሚቻልባቸው ሀገራት ቀዳሚ ሆነች!
በኢትዮጵያ ውስጥ ደስተኛ እና የተረጋጋ ሕይወት ለመምራት የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ከ123 የዓለም ሀገራት በጣም ዝቅተኛው መሆኑን አዲስ ጥናት አረጋገጠ። ‘ሪሚትሊ’ የተባለ ዓለም አቀፍ ተቋም ባወጣው መረጃ መሠረት፣ በኢትዮጵያ ደስተኛ ሕይወት ለመኖር በአማካይ 10,176 ዶላር አመታዊ ገቢ ማግኘት በቂ ነው። ከኢትዮጵያ በመቀጠል ናይጄሪያ እና ሩዋንዳ ከ15 ሺህ ዶላር በታች በሆነ ገቢ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በአንጻሩ በአፍሪካ ከፍተኛው የገንዘብ መጠን የተመዘገበው በግብፅ ሲሆን (59,675 ዶላር ይጠይቃል)፤ በጥናቱ ከተካተቱት 32 የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዳቸውም 100 ሺህ ዶላር አልደረሱም። በአገራቱ መካከል ለሚታየው ለዚህ ከፍተኛ የገንዘብ ልዩነት ዋና ምክንያቶች ተብለው የተጠቀሱት፣ የየሀገራቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን እና ዶላር መግዛት የሚችለው የምርት መጠን (የኑሮ ውድነት) መለያየት ነው።
@Seledadotio

No comments yet.