“ራዕያችሁን ሰዎች ባይረዱት እንኳ መስራታችሁን ቀጥሉ” — ዶክተር ፊን ዲቲሚ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የቴክኖሎጂና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ባለሙያው ዶክተር ፊን ዲቲሚ ታላላቅ ራዕዮችን እውን የማድረግ ጉዞና የሚያስፈልገውን የጽናት መርህ አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ።

ማንኛውም አዲስና ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ሀሳብ ሲጠነሰስ መጀመሪያ ላይ ለሁሉም ሰው አሳማኝ ሆኖ ላይታይ እንደሚችል የጠቆሙት ባለሙያው በስኬት ጉዞ ውስጥ ዋናው ቁልፍ የሰዎች እውቅና ሳይሆን የባለራዕዩ ያልተቋረጠ ቁርጠኝነት መሆኑን ገልጸዋል።

​ዶክተር ፊን እንደገለጹት በጉዞው መጀመሪያ ላይ በርካታ ሰዎች የራዕዩን እውን መሆን ሊጠራጠሩ፣ጥያቄ ሊያነሱ ወይም የቀድሞ መነሻችሁን በማሰብ ስጋቶችን ብቻ አጉልተው ሊመለከቱ ይችላሉ።

ነገር ግን ውጤታማ ለመሆን የሁሉም ሰው መረዳትና አብሮ መሰለፍ ቅድመ ሁኔታ እንዳልሆነ የገለጹት የቴክኖሎጂ ባለሙያው ይልቁንም ዋናው ተግባር በራዕዩ ላይ በማተኮር በየቀኑ በሥራ ላይ መገኘት፣ ዕውቀትን ማሳደግ እና ሀሳብን ወደ ተጨባጭ ተግባር መለወጥ እንደሆነ አስረድተዋል።

በጽናትና በጥረት የሚገነባ ስኬት በሂደት ፍሬ ማፍራት ሲጀምር፣ ትናንት በጥርጣሬ ይመለከቱት የነበሩ አካላት እንኳ ሊክዱትና ሊያልፉት የማይችሉት ግልጽ እውነታ እንደሚሆን አክለው ገልጸዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: