#Ethiopia | ቁራዎች የሞተ የቢጤአቸውን አስከሬን ሲያገኙ ወዲያውኑ ከመብረር ይልቅ በዙሪያው በመሰብሰብና ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮህ አካባቢውን ለረጅም ደቂቃዎች በጥንቃቄ ይመለከታሉ።
ለበርካታ ዓመታት ሳይንቲስቶችን ሲያደናግር የቆየውን ይህንን ባህሪ በተመለከተ የዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ባካሄዱት ጥናት ስብስቡ የኃዘን ወይም የሸኝት ሥነ-ሥርዓት ሳይሆን የሞቱን መንስኤ ለማወቅ የሚደረግ እውነተኛ ምርመራ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በጥናቱ መሠረት ቁራዎቹ ቦታውን በጥንቃቄ በመቃኘት ሊያጋጥም የሚችልን አደጋ ወይም አዳኝ እንስሳ ለመለየት ይሞክራሉ።
እንዲያውም ከሞተው ቁራ ጋር ንክኪ ያለውን የሰው ልጅ ፊት ለዓመታት የመለየትና የማስታወስ አስደናቂ ብቃት ያላቸው ሲሆን በዚህም መረጃውን ለሌሎች መንጋዎቻቸው በማስተላለፍ ከአደገኛ ቦታዎችና ግለሰቦች ራሳቸውን ይጠብቃሉ።
በዓለማችን ካሉ አስተዋይ ወፎች መካከል የሚመደቡት ቁራዎች ውስብስብ ችግሮችን ከመፍታት ባሻገር የሰዎችን ፊት በመለየትና መረጃዎችን ለቢጤዎቻቸው በማጋራት የሚታወቁ ፍጡራን ናቸው።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.