#Ethiopia | በፈረንጆቹ 1896 በእንግሊዝ መዲና ለንደን በወቅቱ ገና አዲስ የነበረው ተሽከርካሪ የሁለት ልጆች እናት የነበረችውን የ44 ዓመቷን ብሪጅት ድሪስኮል ሕይወት ቀጠፈ።
ይህ አጋጣሚ በዓለም ታሪክ የመጀመሪያው የመኪና አደጋ የሰው ሕይወት የጠፋበት አሳዛኝ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል።
ብሪጅት ድሪስኮል ከሴት ልጇ ጋር በመሆን ዘና ለማለት ወደ መዝናኛ ስፍራ በእግረኛ መንገድ ላይ በመጓዝ ላይ እያሉ ነበር አደጋው የደረሰባት።
ጭንቅላቷ ላይ በደረሰባት ከባድ ጉዳት ምክንያት የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ብሪጅት በቦታው ሕይወቷ ሊያልፍ ችሏል።
በወቅቱ አደጋውን የመረመረው የለንደን አቃቤ ሕግ እና መርማሪ ዳኛ ክስተቱን በድንገተኛ አደጋ የተከሰተ ሞት በማለት አሽከርካሪውን ነፃ እንዲወጣ ተወሰነ።
በወቅቱ ዳኛው ውሳኔያቸውን ሲያስተላልፉ ይህ አይነቱ አሰቃቂ አደጋ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ የተከሰተ ሲሆን ዳግመኛም በዓለም ላይ በፍጹም አይከሰትም ብለው ተናገሩ።
ሆኖም የዳኛው ግምት ሳይሳካ ቀርቶ ያ ዕለት እስከ ዛሬ ድረስ ለቀጠለው የትራፊክ አደጋ መነሻ ታሪካዊ ቀን ሆኖ ተመዝግቧል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#london #England
#caraccident #traffic
Source: GetuTemesgen









No comments yet.