የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ ርቀው ለሚገኙ የገጠር አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋፋት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሐዌ ጉዲና ወረዳ የተገነቡ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን አስመርቋል።
ፕሮጀክቶቹ የተገነቡት በቶርበን፣ ባቴ፣ ሐሎ ጎባ እና ሐሮ ኦባ ቀበሌዎች ሲሆን፣ በአጠቃላይ 769 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው ናቸው፡፡
አራቱ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች በድምሩ 900 ኪሎ ዋት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላቸው፡፡
በፕሮጀክቱ 7.74 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር፣ 30.29 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም 10 የዲስትሪቡዩሽን ትራንስፎርመሮች ተተክለው ሥራ ጀምረዋል።
ማህበራዊ ተቋማትን ጨምሮ ከ5 ሺህ 276 በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ የማድረግ አቅም ያላቸው እነዚህ ፕሮጀክቶቹ፤ በአሁኑ ወቅት በአራቱም ቀበሌዎች ከ844 በላይ አባወራዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን እየተገነቡ ከሚገኙ 8 የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ውስጥ 6ቱ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶቹ ከዋናው የኃይል ቋት ርቀው ለሚገኙ የገጠር ማህበረሰቦች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ከማስፋፋት ባለፈ፣ በገጠር አካባቢዎች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ለማጠናከር የሚያግዙ ናቸው።
የፕሮጀክቶቹ ግንባታ የተከናወነውም ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክና ብርሃን ተደራሽነት (ADELE) ፕሮግራም አካል ነው።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት




Source: GetuTemesgen








No comments yet.