#Ethiopia | በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ በእናቶችና ህፃናት ጤና ዳይሬክቶሬት “ከእናቶችና ህጻናት ጉርስ ተቀንሶ ቅንጡ ስልኮች ተገዙ” ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የቆየውን መረጃ በተመለከተ ቢሮው ምላሽ ሰጥቷል ሲል ዶች ኤች ዲ ዘግቧል።
የስልኮቹ ግዢ መፈጸሙን ያረጋገጠው ቢሮው ግዢው ግን በማህበራዊ ሚዲያ እንደሚወራው ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ የተፈጸመ ሳይሆን፣ ከአለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም (WFP) ፕሮጀክት የሥራ ማስፈጸሚያ ወጪ (operation cost) ተቀንሶ ለተቋማዊ የመረጃ ልውውጥ አገልግሎት መሆኑን አስታውቋል።
በፕሮጀክት ውሉ መሠረት እስከ ታችኛው የወረዳ መዋቅር ድረስ ለሚከናወነው የጤና መረጃ ልውውጥ ሥርዓት ከተንቀሳቃሽ ስልኮች በተጨማሪ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ታብሌቶች እና ፓወር ባንኮች ተገዝተው ወደ ሥራ መግባታቸው ተገልጿል።
ንብረቶቹ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡና የግዢው ሂደት ግልጽ እንዲሆን ሙሉ በሙሉ ከመንግስታዊው ተቋም ኢትዮ ቴሌኮም የተገዙ ሲሆን፣ እነዚህ ቁሳቁሶች በጨታ፣ መኤኒት ጎልዲያ፣ ዛባ ጋዞ፣ ጌና እና ሎማ ቦሳ ወረዳዎች ለሚገኙ የጤና መዋቅሮች አገልግሎት እንዲውሉ መደረጉም ተብራርቷል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.