“ይህ እኔን ሜዳ ውስጥ የምታዩበት የመጨረሻ ዓመት ነው”

- Advertisement -
Sidebar AD

— ክርስቲያኖ ሮናልዶ

#Ethiopia | ​የ41 ዓመቱ የዓለማችን የእግር ኳስ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከደማቅና ስኬታማ የጨዋታ ዘመኑ በኋላ ይህ የውድድር ዓመት የመጨረሻው ሊሆን እንደሚችል አስታወቀ።

በቅርቡ ከረጅም ጊዜ አጋሩ ጆርጂና ሮድሪጌዝ ጋር ጋብቻ የፈጸመው ፖርቹጋላዊው አጥቂ ከእግር ኳስ በኋላ ያለው ጊዜ በቤተሰቡ ላይ ያተኮረ እንዲሆን ማቀዱንና ላለፉት 25 ዓመታት በብዙ መስዋዕትነት ያተረፈውን ስኬት ለማጣጣም እንደሚፈልግ ገልጿል።

​የአምስት ጊዜ የባሎንዶር እና የአምስት ጊዜ የቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ሮናልዶ ከአሁኑ ክለቡ አል ናስር ጋር ያላበቃ የውል ጊዜ የሚቀረው ሲሆን ከሜዳ ሲሰናበት ታሪክ ጥሎ ማለፍ እንደሚፈልግ ተናግሯል።

በጨዋታ ዘመኑ 1,000 ግቦች ለማስቆጠር የ24 ግቦች ብቻ የሚቀሩት ኮከቡ፣ ከእግር ኳስ በኋላ የመዝናናት፣ የጉዞና ከተለያዩ ስፖርቶች ጋር የመቆየት ፍላጎት እንዳለው ጠቁሟል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: