#Ethiopia | ቻይና ጃፓንን እና ጀርመንን በመበለጥ በዓለም የአንደኝነት ደረጃን ጨበጠች።
የዓለማችንን የመኪና ኤክስፖርት ገበያን ለሁለት አስርት አመታት በበላይነት ሲመሩ የነበሩት ጃፓን እና ጀርመን ቦታቸውን ለቻይና አስረክበዋል።
ቻይና በከፍተኛ ምርት የዓለማችን ቀዳሚዋ የመኪና ላኪ ሀገር መሆኗን አረጋግጣለች።
በ2024 ቻይና በዓመት 5.5 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎችን ወደ ውጭ የመላክ አቅም የነበራት ሲሆን አሁን አቅሟን በከፍተኛ መጠን አሳድጋለች።
ሀገሪቷ የኤክስፖርት አቅሟን በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ በዓመት ከ7 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎች በላይ ወደ ተለያዩ ሀገራት መልክ ችላለች።
አሁን ባሉ መረጃዎች መሠረት ጃፓን 4.2 ሚሊዮን እና ጀርመን 3.4 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎችን በመላክ ቻይናን በመከተል ላይ ይገኛሉ።
በአለም የኤሌክትሪክ እና የፕላግ ኢን ሃይብሪድ ተሽከርካሪዎች ፍላጎት እያደገ በመምጣቱ ነው የቻይና አቅም እንዲያድግ ምክንያት የሆነው ሲል ሲጂቲኤን ያስነበበው።
በዚህም ቻይና ዓለም አቀፍ የመኪና ገበያን በአጭር ጊዜ ውስጥ የተቆጣጠረች የመጀመርያዋ ሀገር አስብሏታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#China #Japan #Germany
#car #market #export #industry #technology #electric
Source: GetuTemesgen









No comments yet.