ልብ ለልብ በአንድ አውሮፕላን

- Advertisement -
Sidebar AD

ሐኪም አለ? ሲባል 15 የልብ ስፔሻሊስቶች ተነሱ!

#Ethiopia | በበረራ ላይ የልብ ህመም ያጋጠማት እናት በ15 የልብ ስፔሻሊስት ዶክተሮች ተረድታ ከሞት ተረፈች።

ለሴት ልጅዋ ሠርግ ወደ ፍሎሪዳ በመጓዝ ላይ የነበረችው የ67 ዓመቷ እንግሊዛዊት ዶሮቲ ፍሌቸር በአየር ላይ እያለች በድንገት በልብ ሕመም ታማ እራሷን ትስታለች።

የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ከተሳፋሪዎች መካከል የመጀመርያ እርዳታ መስጠት የሚችል ሐኪም አለ? ሲሉ ጥሪ አሰሙ።

ወዲያው ማንም ያልጠበቀው አስደናቂ አጋጣሚ ተከሰተ።

15 ተሳፋሪዎች በአንድ ጊዜ ከመቀመጫቸው ብድግ አሉ።

አጋጣሚ ሆኖ 15ቱም ተሳፋሪዎች በኦርላንዶ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የልብ ሕክምና ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ይጓዙ የነበሩ የልብ ስፔሻሊስቶች (Cardiologists) ነበሩ።

ሐኪሞቹ በአውሮፕላኑ ውስጥ ባገኙት የመጀመሪያ ህክምና መስጫ መሳርያ በመጠቀም ወዲያውኑ የድንገተኛ ህክምና እርዳታ መስጠት ጀመሩ።

አውሮፕላኑም በአቅራቢያው በሚገኝ አየር ማረፊያ እንዲያርፍ ለአብራሪዎቹ ጥብቅ መመሪያ ተሰጣቸው።

በዚሁ መሠረት አውሮፕላኑ አቅጣጫውን በመቀየር በቻርሎት ሰሜን ካሮላይና እንዲያርፍ ተደረገ።

የ67 ዓመቷ የልብ ታካሚ ወዲያውኑ ወደ ህክምና ማዕከል ተወስዳ ሙሉ በሙሉ ከህመሟ ማገገም ችላለች።

ታካሚዋ ከህመሟ ብቻ አይደለም የዳነችው የሴት ልጅዋን ሰርግም በደስታ ለማክበር በቅታለች።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#heartattack #flight #Florida.
#Cardiologists #Doctor


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: