በአንቺ አማላጅነት፣በልጅሽ ምሕረት የታምንሁ ነኝ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነቷና ተራዳኢነቷ በብዙ መልኩ ዛሬም ድረስ ያልተለየን የዘለዓለም ቃል ኪዳን የተገባላትና በቃል ኪዳኗም አማልዳ የምታስምር ናት፡፡ በመዝሙር 88÷3 “ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ለመረጣቸው ቃል ኪዳን የሰጣቸው አምላካችን እግዚአብሔር ማደሪያው ትሆን ዘንድ ለመረጣት ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያም ከሌሎች ቅዱሳን በተለየ ይህን ቃል ኪዳን አብዝቶ ሰጥቷታል፡፡ ”መታሰቢያዋን የሚያደርግ፣ ስሟን የሚጠራ፣ ለድሆችና ለችግረኞች እስከ ቀዝቃዛ ውኃ የሚሰጥ” የአማላጅነት የእናትነት ቃል ኪዳን በነፍስም በስጋም ይጠብቀዋል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት “በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” ሲል በመዝሙር 44÷9 እንደገለጸው ከፍጥረት ሁሉ በላይ ነችና በቀኙ ቆማ በተሰጣት ቃልኪዳን ታማልደናለች፡፡
የዐሥራት ልጆቿ እኛ ክርስቲያኖችም ዘወትር “ንጽሕት ድንግል ማርያም የታመነች አምላክን የወለደች ናት። ለሰዎች ልጆችም የምሕረት አማላጅ ናት እንላለን። የቅዱስ ኤፍሬምን አንደበት አንደበታችን አድርገንም ኃጥአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ልጅሽ ወደ ክርስቶስ ለምኝልን” እያልን እናመሰግናታለን እንለምናታለን። ከአባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ጋርም በእሑድ አርጋኖን “ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ! እታመንሻለው፤ ከተሠወረው መከራ፣ በግልጽ ከሚመጣብኝ ጥፋት ሁሉ በዚህ ዓለም እንድታድኚኝ። በሚመጣውም ዓለም ከገሃነመ እሳት ጥርስ ማፋጨት ጽኑ ለቅሶም ካለበት፣ ከሚያስጨንቅ መቅሠፍትም ትሠውሪኝ ዘንድ፣ እኔም በአንቺ አማላጅነት፣ በልጅሽ ምሕረት የታምንሁ ነኝ። በፈረሰኞች ሰልፍ በሠረገላም መንኮራኩር የምታመን አይደለሁም በአንቺና በልጅሽ እታመናለው እንጂ።” እያልን እንማጸናታለን፡፡ እናታችን ቅድስተ ቅዱሳን ጸሎታችንን ትስማን
እኛም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋዋ ከሞትና መቃብር መለየትና ማረግን አስመልክተን በምንጾመው ጾመ ፍልሰታ ለተቸገሩት ድጋፍ በማድረግ የበረከት ስራን እንስራ።በከባድ ንፋስና ዝናብ ምክንያት ቤተ መቅደሱ ለፈረሰበት “ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም” ድጋፍ በማድረግ ቤተ መቅደሱን መልሰን እንስራ፤በድርቅና በርሃብ በከባድ ፈተና ውስጥ ለሚገኙት መነኮሳት እንድረስላቸው።ለመነኮሳቱ ምግብና መሠረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት በአቅማችን እንረባረብ። በመስጠት ነፍሳችንን ደስ እናሰኛት፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡- 1000766349227
አቢሲንያ ባንክ ፡- 262281132
ለበለጠ መረጃ:- 0944672222 ወይም 0916106921
Source: GetuTemesgen









No comments yet.