#Ethiopia | በጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በአንድ ወሊድ አራት ህፃናትን በሰላም ያገላገለችው የ26 ዓመት ወጣት እናት ከተደረገላት ተከታታይ የህክምና ክትትል በኋላ ከነልጆቿ ሙሉ ጤንነቷ ተጠብቆ ወደ ቤቷ ተሸኝታለች።
አዲስ አበባ ጤና ቢሮ ነሀሴ 12 ቀን 2018 ዓም ባወጣው መረጃ መሠረት እናቲቱ ባለፈው ሳምንት በሆስፒታሉ ተገቢውን የወሊድ ህክምና አግኝታ ከተገላገለች በኋላ ላለፉት ስምንት ቀናት ከህፃናቱ ጋር አስፈላጊው የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቷል።
ህፃናቱ በተወለዱበት ወቅት የነበራቸው ክብደት ከ1 ነጥብ 4 እስከ 1 ነጥብ 9 ኪሎ ግራም የነበረ በመሆኑ በጨቅላ ህፃናት ማጠናከሪያ ክፍል ውስጥ በማሞቂያ ገብተው ልዩ የህክምናና የነርሲንግ ክትትል እንዲያገኙ ተደርጓል።
በተደረገላቸው ከፍተኛ የህክምና እንክብካቤ እና የቅርብ ክትትል አራቱም ህፃናት እንዲሁም እናታቸው በጥሩ ጤንነት ላይ በመገኘታቸው የሆስፒታል ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#TiruneshBeijingHospital #HealthSector #NewbornCare #EthiopianHealth #AddisAbabaHealth #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Source: GetuTemesgen









No comments yet.