*በጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል አራት ህፃናትን በሰላም የተገላገለችው እናት

- Advertisement -
Sidebar AD

በጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ለአራት ህፃናት እናት የሆነችው የ26 ዓመት ወጣት፣ በሆስፒታሉ ሲደረግላት የቆየውን የህክምና ክትትል አጠናቃ ከልጆቿ ጋር በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ትገኛለች።

ባለፈው ሳምንት አራቱን ህፃናት በሰላም የተገላገለችው ወጣት እናት፣ ላለፉት ስምንት ቀናት በህክምና ባለሙያዎች በተደረገላት የቅርብ ክትትል ሙሉ በሙሉ በጥሩ የጤና ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ህፃናቱ በተወለዱበት ወቅት የነበራቸው ክብደት ከ1.4 እስከ 1.9 ኪሎ ግራም የነበረ በመሆኑ፣ በጨቅላ ህፃናት ማጠናከሪያ ክፍል በማሞቂያ (Incubator) ውስጥ ገብተው አስፈላጊው ከፍተኛ የህክምና እና የነርሲንግ ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቷል።

በተደረገላቸው የተቀናጀ እና የቅርብ እንክብካቤ አራቱም ህፃናት እንዲሁም እናታቸው በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2