#Ethiopia | ለአትሌቲክሱ ትልቅ ኪሳራ መሆኑን ረዳት ኮሚሽነር ሁሴን ሼቦ ገለጹ
µ በአሜሪካ በተካሄደው ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተሳትፎ ለማድረግ ከተጓዘው የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን ውስጥ ሶስት አሰልጣኞች እና አራት አትሌቶች ወደ ሀገር ሳይመለሱ መቅረታቸውን ተከትሎ ረዳት ኮሚሽነር ሁሴን ሼቦ ጥበቃና ክብካቤ ካልተደረገላቸው ተመሳሳይ ክስተቶች እንደሚቀጥሉ አሳስበዋል።
በፖርትላንድ እና ቺካጎ አየር መንገድ አባላቱ ተለይተው የቀሩ ሲሆን የቡድኑ መሪዎች ለፖሊስ አመልክተው ቢፈልጉም ሊያገኟቸው አልቻሉም።
የፌዴሬሽኑ አመራሮች አግኝተው ለማነጋገር ቢሞክሩም እስካሁን የተመለሰ የለም።
ረዳት ኮሚሽነር ሁሴን ሼቦ በሁኔታው ማዘናቸውን ገልጸው አሰልጣኞቹ ከፍተኛ የትምህርትና የሙያ ደረጃ ያላቸው በመሆናቸው ማጣታቸው ለአትሌቲክሱ ትልቅ ጉድለት ነው ብለዋል።
ከአሰልጣኞች አያያዝ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች ስር የሰደዱ መሆናቸውን በመጥቀስ እንደ ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ያሉ ትልልቅ ባለውለተኞች እንኳን ተገቢውን ክብር ሳያገኙ ማለፋቸውን አስታውሰዋል።
በአሁኑ ወቅት ለአሰልጣኞች የሚከፈለው ደሞዝ ከጊዜው የኑሮ ውድነት ጋር የማይመጣጠንና ዝቅተኛ መሆኑን የተናገሩት አሰልጣኙ ቀደም ሲል ይሰጡ የነበሩ ማበረታቻዎች መቅረታቸው አሰልጣኞችን ወደ ስደት እንደሚገፋ ገልጸዋል።
የአሰልጣኞችን አያያዝ የማያሻሽልና ተገቢውን ክብር የማይሰጥ አሰራር ካልተቀየረ አትሌቶችና አሰልጣኞች የተሻለ ህይወት ፍለጋ መሰደዳቸው የሚቀጥል መሆኑን አሳስበዋል።
በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)
#athletics #ethiopianathletics #sports #husseinshebo #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen








No comments yet.