ፓትሪክ ቪየራ የቴራንጋ አንበሶችን ተረከበ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቀድሞውን የፓፕ ቲያው ቦታ ለመተካት ፓትሪክ ቪየራን በዋና አሰልጣኝነት መሾሙን ይፋ አድርጓል።

የቀድሞ የፈረንሳይና የአርሰናል የመሀል ሜዳ ተጫዋች ፓትሪክ ቬየራ ኒውዮርክ ሲቲ፣ ኒስ፣ ክሪስታል ፓላስ፣ ስትራስቦርግ እና ጄኖዋን በአሰልጣኝነት አሰልጥኗል።

የቀድሞው የአርሰናል እና የፈረንሳይ አማካይ ፓትሪክ ቪየራ የተወለደው በሴኔጋል ቢሆንም የተጫወተው ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ነው።

ይህ ሹመት ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ እና ለቀጣይ ትልልቅ ውድድሮች ሴኔጋልን በጠንካራ ሁኔታ ለማዘጋጀት ያለመ ነው ተብሏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Senegal #patricVieira
#Headcouch #Africa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1