6 ህገወጥ ኢትዮጵያውያንን በመኪና ሲያጓጉዝ የነበረው ሱዳናዊ 42 ሚሊዮን የኢትዮጵይ ብር እና የ15 ዓመት እስራት ሊቀጣ ነው:…

- Advertisement -
Sidebar AD
6 ህገወጥ ኢትዮጵያውያንን በመኪና ሲያጓጉዝ የነበረው ሱዳናዊ 42 ሚሊዮን የኢትዮጵይ ብር እና የ15 ዓመት እስራት ሊቀጣ ነው::
በጃዛን ክልል 6 ኢትዮጵያውያንን በህገ-ወጥ መንገድ ሲያጓጉዝ የነበረ ሱዳናዊ በቁጥጥር ስር ዋለ
በሳዑዲ አረቢያ የጃዛን ክልል የመጅሃዲን ጠቅላይ መመሪያ የጥበቃ አባላት የሀገሪቱን የድንበር ደህንነት ህግ በመጣስ በህገ-ወጥ መንገድ የገቡ 6 ኢትዮጵያውያንን በሲቪል መኪና ሲያጓጉዝ የነበረ አንድ የሱዳን ዜጋ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታውቀዋል።
የተያዘው አጓጓዥ ጉዳዩ በህግ እንዲታይ ለዐቃቤ ህግ የተላከ ሲሆን፤ ህገ-ወጥ የድንበር ጥሰት የፈፀሙት ኢትዮጵያውያንም አስፈላጊው የህግ ሂደት
ከተፈፀመባቸው በኋላ ለሚመለከተው አካል ተልከዋል።
የመጅሃዲን ጠቅላይ መመሪያ ቃል አቀባይ እንዳስገነዘቡት፤ የድንበር ደህንነት ህግ ተጣሾች ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንዲገቡ
* ማመቻቸት፣
* ማጓጓዝ፣
* መጠለያ መስጠት ወይም ማንኛውንም አይነት የትብብር ድጋፍ ማድረግ በህግ ያስጠይቃል።
በዚህ የወንጀል ድርጊት ላይ የተሰማሩ አካላት ላይ የሚከተሉት ከባድ ቅጣቶች ይጣላሉ፦
1. እስከ 1 ሚሊዮን የሳዑዲ ሪያል (በወቅቱ የምንዛሬ ተመን ከ42 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ)።
2. እስከ 15 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት።
3. በህገ-ወጥ ዝውውሩ ወቅት ጥቅም ላይ የዋለው የትራንስፖርት ተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ ይወረሳል።
አስፈላጊውን ህጋዊ የጉዞ ሰነድ ሳይይዙ የሚደረግ የድንበር ጥሰትና ህገ-ወጥ ዝውውር ለከባድ የእስራትና የገንዘብ ቅጣት የሚዳርግ በመሆኑ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልእክት ተ አስተላልፏል።
Via Saudi Gazette
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2