ALLIKE Furniture እና ሜሪ ዲዳ ዲሳሳ የጋራ የብራንድ አምባሳደርነት አጋርነታቸውን አራዘሙ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኢትዮጵያ የቤት እቃዎች አቅርቦት ዘርፍ ቀዳሚ ስም ያለው ALLIKE Furniture እና የሜሪ ዲዳ Promotion and Events መስራችና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዋ ሜሪ ዲዳ ዲሳሳ ላለፉት ሦስት ዓመታት በጋራ ሲያከናውኑ የቆዩትን የማስተዋወቅና የዲጂታል ሚዲያ ስራዎች ውጤታማነት በመገምገም የብራንድ አምባሳደርነት ውላቸውን በጥበብ አድሰዋል።

ዛሬ በይፋ ይፋ የተደረገው ይህ የስምምነት እድሳት ሁለቱ ወገኖች የነበራቸውን ጠንካራ የላቀ የስራ ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ሲሆን፣ ተቋሙ በቤቴል አካባቢ አዲስ የከፈተውን ዘመናዊ ቅርንጫፍ ለደንበኞቹ ያስተዋወቀበትም አጋጣሚ ሆኗል።

ድርጅቱ ከሜሪ ዲዳ ጋር ያለውን አጋርነት ለመቀጠል የወሰነው በህዝብ ዘንድ ባላት ሰፊ ተቀባይነት ብቻ ሳይሆን በስራ ትጋቷ፣ መልካም ስነምግባሯ እና ከማህበረሰቡ ጋር ባላት ጥልቅ ትስስር ምክንያት መሆኑን አስታውቋል።

በመድረክ መሪነቷ፣ በተዋናይነቷ፣ በስራ ፈጣሪነቷ እንዲሁም በOBN እና በYouTube በሚሰራጨው “Kaameettii Podcast” ፕሮግራሟ የምትታወቀው ሜሪ ዲዳ፣ የድርጅቱን እሴቶች ለህዝብ በማድረስ ረገድ የጎላ ሚና ተጫውታለች።

በቀጣይም ሁለቱ ወገኖች በፈጠራ፣ በጥራትና በመተማመን ላይ የተመሰረቱ በርካታ ማስተዋወቂያዎችን እና የዲጂታል ይዘቶችን ለህዝብ ለማቅረብ ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።

#ALLIKEFurniture #MeriDida #BrandAmbassador #BusinessUpdate #AddisAbabaBusiness #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1