ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በአስከሬን ንግድ ቅሌት ምክንያት 53 ሚሊየን ዶላር ሊከፍል ነውየሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ቤ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በአስከሬን ንግድ ቅሌት ምክንያት 53 ሚሊየን ዶላር ሊከፍል ነው
የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ቤት ለምርምር የተበረከቱ አስከሬኖች በህገ-ወጥ መንገድ መሸጣቸውን ተከትሎ ከሟች ቤተሰቦች የቀረበበትን ክስ ለመፍታት የ53 ሚሊየን ዶላር ክፍያ ስምምነት ላይ ደርሷል።
የዝነኛው ትምህርት ቤት የቀድሞ የሬሳ ማቆያ ክፍል ሥራ አስኪያጅ ከ2018 እስከ 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ የሟቾችን የሰውነት ክፍሎች በመስረቅ በጥቁር ገበያ ሲሸጡ እንደነበር አምነዋል።
ግለሰቡ የአካል ክፍሎቹን በፔንስልቬንያ እና ማሳቹሴትስ ለሚገኙ ገዢዎች በመስመር ላይ ይሸጡ እንደነበር በክሱ ተገልጿል።
በዚህ ድርጊት ሳቢያ የ58 ዓመቱ ሎጅ የስምንት ዓመት እስራት የተፈረደባቸው ሲሆን፤ባለቤታቸውም በተባባሪነት የአንድ ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል።
ዩኒቨርሲቲው በቦስተን ፍርድ ቤት በደረሰው በዚህ ስምምነት መሠረት፣ ገንዘቡ ፍርድ ቤቱ ካጸደቀው በኋላ ድርጊቱ ለደረሰባቸው ቤተሰቦች እንደ ማካካሻ የሚከፋፈል ይሆናል።
ቤተሰቦቹ ዩኒቨርሲቲው ይህንን ግዙፍ ጥፋት ለዓመታት ችላ ብሎታል በሚል ክስ መስርተው የነበረ ቢሆንም፤አሁን በተደረገው ስምምነት ክሱ እልባት ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1