#Ethiopia | የዓለማችን ባለሀብቶች የሀብት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ እያሳየ እንደሚገኝ ፎርብስ አስታወቀ።
በተለይም በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስ እና በኃይል ዘርፍ ላይ የተሰማሩት የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለሀብቶች ሀብታቸውን በከፍተኛ ፍጥነት እያሳደጉት ይገኛሉ ነው ያለው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ቢሊየነሮች አጠቃላይ ሀብት ከ14 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ማለፉን የፎርብስ መረጃ ያመለክታል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ብቻ የዓለማችን ሀብታሞች ሀብት በየቀኑ በቢሊዮኖች ዶላር በሚቆጠር መጠን ማደጉንም ገልጿል።
ይህም ከዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ድቀት እና የዋጋ ንረት ጋር ሲነጻጸር የሚቃረን ሆኖ ተገኝቷል።
ከዚህ የሀብት መጠን ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ሀብት የተቆጣጠሩት 100 ባለፀጎች ብቻ ናቸው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የባለሀብቶች ሀብት በየጊዜው እያደገ ቢመጣም ይህ ሁኔታ በዓለም ኤኮኖሚ ላይ የራሱን አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል።
በአንድ በኩል ለቴክኖሎጂ እና ለፈጠራ ስራዎች ትልቅ ኢንቨስትመንት ሲፈጥር በሌላ በኩል ደግሞ በሀብታሞች እና በድሆች መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት የበለጠ እንዳሰፋው ተገልጿል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Forbes #richest #peoples
#industry #technology #entrepreneur
Source: GetuTemesgen









No comments yet.