የዜሮ ዓመት የስራ ልምድ ቅጥር እንዲቀር የሚል ምክረ-ሐሳብ ከስምምነት ላይ ተደረሰበትእየተገባደደ በሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ጉ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የዜሮ ዓመት የስራ ልምድ ቅጥር እንዲቀር የሚል ምክረ-ሐሳብ ከስምምነት ላይ ተደረሰበት
እየተገባደደ በሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ተሳታፊዎች የስራ ቅጥርን በተመለከተ «የዜሮ ዓመት የስራ ልምድ ቅጥር እንዲቀር» የሚል ምክረ-ሐሳብ አቅርበው ከስምምነት መድረሳቸው ተገለፀ።
በተጨማሪም በጉባዔው ውይይት ወቅት ሁሉም ትምህርት ቤቶች ለሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በነጻ እንዲያቀርቡ የሚል አዎንታዊ ምክረ-ሐሳብ ተነስቶ ስምምነት ከተደረሰባቸው ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳል።
በአሁኑ ወቅት 500 አባላት ባሏቸው 8 ቡድኖች ተከፋፍለው ውይይታቸውን በማጠቃለል ላይ የሚገኙት ተወካዮች፣ በአብዛኞቹ አጀንዳዎች ላይ ተወያይተው ወደ መስማማት መምጣታቸው ተገልጿል።
ይሁን እንጂ እስካሁን መስማማት ያልተቻለባቸው እና በይደር እንዲቆዩ የተደረጉ አጀንዳዎች የትኞቹ እንደሆኑ እስካሁን ይፋ አልተደረገም።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ተወካዮቹ በምክክሩ ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ የቀረቡትን ምክረ-ሐሳቦች በማጠናከር አጠቃላይ ወጥ የሆነ ሰነድ የማዘጋጀት ሥራ ጀምረዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1