የግብፁ አሰልጣኝ ሁሳም ሀሰን በሁለት ሚስቶቻቸው ግጭት ራሳቸውን ስተው ሆስፒታል ገቡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ እና የሀገሪቱ እግር ኳስ ታዋቂ ስም የሆኑት ሁሳም ሀሰን በሆቴል ውስጥ በሚስቶቻቸው መካከል በተነሳ የኃይል ግጭት ወቅት ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተሰማ።

የጀርመኑ ‘ቢልድ’ ጋዜጣ እንደዘገበው አሰልጣኙ በሁለቱ ሚስቶቻቸው መካከል በተፈጠረ ጭቅጭቅ እና ግብግብ መሃል በመገኘታቸው ለዚህ ድንገተኛ የጤና መታወክ ተዳርገዋል።

​በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየተሰራጨ የሚገኘው ተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚያሳየው በሆቴሉ ውስጥ በሁለቱ ሰዎች መካከል የተጀመረው የቃላት ምልልስ በፍጥነት ወደ ከባድ እርስ በርስ ድብደባ አድጓል።

በቦታው የነበሩ እማኞች እንደገለጹት በግጭት ወቅት በቅርብ ያገኙትን ቁሳቁሶች ጭምር በመወራወር ወደ ከፋ ደረጃ የተሸጋገረ ሲሆን ሁኔታውን ለማረጋጋትና ሁለቱን ሰዎች ለመለያየት የሆቴሉ ጥበቃ አባላት ጣልቃ ለመግባት ተገደዋል።

​በዚህ ድንገተኛና ውጥረት የነገሰበት ሁከት መሃል የነበሩት አሰልጣኝ ሁሳም ሀሰን በድንገት ራሳቸውን ስተው መሬት ላይ ወድቀዋል። ወዲያውኑ ወደ አቅራቢያ ወደሚገኝ ሆስፒታል ተወስደው አስፈላጊው የሕክምና እርዳታ የተደረገላቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት የጤና ሁኔታቸው በጥሩና በአስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

አሰልጣኙ በ1994 ዓ.ም ያገቧት ሁወይዳ አል-ገራባዊ እና ከ20 ዓመታት በኋላ ያገቧት ዳና አዳም የተሰኙ ሁለት ሚስቶች እንዳሏቸው ይታወቃል።

​በግብፅ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ እጅግ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑት ግለሰቦች አንዱ የሆኑት ሁሳም ሀሰን በ2026 የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ውድድር የግብፅን ብሔራዊ ቡድን እስከ ፕሌይ-ኦፍ ደረጃ ማድረስ የቻሉ ስኬታማ ባለሙያ ቢሆኑም አሁን ግን ከሜዳ ውጪ በቤተሰብ ጉዳይ ያጋጠማቸው ይህ ክስተት የመገናኛ ብዙሃን እና የፓፓራዚዎችን ትኩረት ስቧል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2