”ለመማር ብርጭቋችን አይሙላ ” – ወ/ሮ ሳምራዊት ሞገስ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ፣ በአትክልት እና በአበባ እርሻ ልማት ውስጥ የረጅም ዓመታት ልምድ ያዳበሩት ወ/ሮ ሳምራዊት ሞገስ ከመሪ ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ በስኬት፣ በንግድ መሪነትና በህይወት ፍልስፍናቸው ዙሪያ ሀሳቦችን አጋርተዋል።

ወ/ሮ ሳምራዊት በንግግራቸው እንደገለጹት፣ ማንኛውም ሰው ውስጣዊ ፍላጎትና ስሜት ካለው በህይወቱ ያሰበውን ማሳካት ይችላል።

በዘርፉ በርካታ ዓመታትን ያሳለፉ ቢሆንም አሁንም “ሁሉንም አውቃለሁ” በሚል ስሜት ሳይሆን ከጊዜው ጋር አብሮ ለመራመድ ሁልጊዜ ለመማር ዝግጁ መሆን እንደሚገባና መማር የማያልቅ ሂደት መሆኑን አብራርተዋል።

​በንግድ ዓለም ስላላቸው ልምድ ሲያብራሩም፣ ማንኛውም ሰው ወደ ንግድ ስራ ከመግባቱ በፊት መሰረታዊ የሂሳብ አያያዝ ( accounting) እውቀት ሊኖረው እንደሚገባ አሳስበዋል።

እሳቸው በወቅቱ ይህ እውቀት ሳይኖራቸው ወደ ቢዝነስ በመግባታቸው ጉዞው ቀላል እንዳልነበር በመግለጽ የሂሳብ ባለሙያዎች ለንግድ ድርጅቶች ስኬት እንደ ጀርባ አጥንት የሚቆጠሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በስራ እና በሰው ግንኙነት ውስጥ ግልጽነትና ነገሮችን ፊት ለፊት የመነጋገር ባህል መኖሩ ለችግሮች ፈጣን መፍትሄ እንደሚያስገኝ የገለጹት ወ/ሮ ሳምራዊት ይህ አካሄድ አንዳንዴ ከሰዎች ጋር ባያስማማ እንኳ ለስራ ውጤታማነትና ለተቋማት ዕድገት ወሳኝ መሆኑን አስምረውበታል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1