#Ethiopia | ከቦንጋ ወደ ጠሎ በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በጠሎ ወረዳ በጋ ቀበሌ ልዩ ቦታ ላይ በመገልበጡ ምክንያት በሰዎች እና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።
በደረሰው አደጋ በ3 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እንዲሁም በ11 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን የወረዳው ትራፊክ ስራ ሂደት አስተባባሪ ረዳት ኢንስፔክተር ሙሉጌታ በዛብህ ገልጸዋል።
የአደጋው መንስኤ በአሁኑ ወቅት በመጣራት ላይ እንደሚገኝና ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችም ወደ ህክምና ተቋም ተወስደው አስፈላጊው እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተመላክቷል።
#Kaffa #Tello #TrafficAccident #SouthwestEthiopia #EthiopianPolice #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Source: GetuTemesgen









No comments yet.