በአጥር ግቢ ዘለው በመግባት የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 4 ተጠርጣሪዎች ከነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

- Advertisement -
Sidebar AD

ዳዊት መብራቱ፣ ናትናኤል በላይ፣ ኃፍቱ ደበለው እና አሸብር ደስታው የተባሉ ተጠርጣሪዎች የቤት በር ሰብሮ ስርቆት ወንጀሉን የፈፀሙት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሰሚት ዋሽንግተን ሰፈር እንዲሁም በወረዳ 2 አቤም ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በተለያየ ቀን እና ሰዓት ነው።

የመኖሪያ ግቢ የደህንነት የኤሌክትሪክ መስመር በመቁረጥና በአጥር ዘለው በመግባት የተለያዩ ንብረቶችን ስርቆት ፈፅመው መሰወራቸው መረጃ የደረሰው በክፍለ ከተማው የመሪና አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው የምርመራ ማጣራት ዳዊት መብራቱ፣ ናትናኤል በላይ እና ኃፍቱ ደበላው የተባሉ ተጠርጣሪዎችን እንዲሁም የተሰረቁ ንብረቶችን የሚቀበላቸውን አሸብር ደስታው የተባለው ግለሰብን ከ3 ቴሌቭዥኖች ፣ የፕሌይ ስቴሽን መጫወቻዎች እና ላፕቶፕ ጋር በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ኮሽም ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ/ም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ባደረገው ምርመራ ማስፋት ተግባር ባልታወቀ ቀንና ሠዓት በየካና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ተመሳሳይ ወንጀሎችን መፈፀማቸውን ያመኑ ሲሆን በክፍለ ከተማው በፈፀሙት የቤት በር ሰብሮ ስርቆት ወንጀል በሁለት የምርመራ መዝገቦች የግል ተበዳዮች በአካል ቀርበው ምስክርነታቸውን የተሰጡ በመሆኑ የክፍሉ አቃቤ ህግ በመዝገቦቹ ላይ ክስ መስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኝ መሆኑም ተገልጿል።

መሰል የወንጀል ድርጊት ተፈፅሞብኛል የሚሉ የግል ተበዳዮች በመሪ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ንብረታቸውን መምረጥ እንደሚችሉ የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ህብረተሰቡ የመኖሪያ ቤቱን ቁልፍ በተገቢው ሊያጠናክር እንደሚገባና በአካባቢው ያሉ የቅጥር ጥበቃዎችን በማነቃቃት ጥንቃቄ ሊያደረግ እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

Addis Ababa Police






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2