በ27 የወሊድ ሂደቶች ብቻ 69 ልጆችን ለዓለም ያበረከተችው ሩሲያዊት እናት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በ18ኛው ክፍለ ዘመን በሩሲያ ሹያ በተባለች የገጠር ቀበሌ ትኖር የነበረችው ቫለንቲና ቫሲሊየቫ የያዘችው የዓለም አስደናቂ ታሪክ ለብዙ ዘመናት በስሟ ተመዝግቦ ይገኛል።

ይህች እናት በተፈጥሮአዊ የገጠር ህይወት ውስጥ ሆና ዘመናዊ የህክምና እርዳታ እና ተገቢ የእናትነት እንክብካቤ በሌለበት ወቅት በ27 ምጥ ብቻ 69 ልጆችን በሰላም መውለዷ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ድንቅነቱን ጥሎ አልፏል።

ታሪኩ የተከሰተው በ18ኛው ክፍለ ዘመን እንደመሆኑ መጠን በወቅቱ የነበረው አነስተኛ የህክምና ደረጃ ጉዳዩን የበለጠ አስገራሚ ያደርገዋል።

ቫለንቲና በ40 ዓመታት የትዳርና የእናትነት ጊዜዋ ከ1725 እስከ 1765 ባሉት ዓመታት ውስጥ በአንድም አጋጣሚ 69 ልጆች ብቻ ወልዳ አታውቅም።

16 ጊዜ ሁለት መንትዮችን በመውለድ 32 ልጆች 7 ጊዜ ሦስት መንትዮችን በመውለድ 21 ልጆች 4 ጊዜ አራት መንትዮችን በመውለድ 16 ልጆች አበርክታለች።

የጊነስ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ እስከ ዛሬ ድረስ ይህንን ዘገባ በአንዲት እናት የተወለዱ ከፍተኛ የልጆች ቁጥር አድርጎ በይፋ ተቀብሎታል።

ድርጊቱ ከረጅም ጊዜ በፊት የተፈጸመ በመሆኑ የዘመኑ የሳይንስና የሕክምና ተመራማሪዎች ዝርዝር ሁኔታዎችን በዘመናዊ መንገድ ለማረጋገጥ ቢቸገሩም በወቅቱ በተዘጋጁ ሃይማኖታዊና መንግስታዊ ሰነዶች የታሪኩ እውነተኛነት በበቂ ሁኔታ ተረጋግጧል።

ሔኖክ ወ/ብርኤል

#Ethiopia #Russia #Moscow #GuinnessWorldRecords #Russianwoman #birth #twins #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1