አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ
#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ጽሕፈት ቤት የደብረ ታቦርን በዓል በተለያዩ ኹነቶች ከከተማው ወጣቶች ጋር በድምቀት ማክበሩን አሳወቀ።
በበዓሉ አከባበር ላይ የቢሮ ከፍተኛ አመራሮች፣ የወጣት ማህበራት አባላት፣ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ተጠቃሚዎች እና የከተማዋ ወጣቶች ተገኝተዋል።
በበዓሉ መርሐግብር ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ሀይለጊዮርጊስ እንደገለጹት፤ እንደዚህ ያሉ ድንቅ የሆኑ የኢትዮጵያውያን ሀገር በቀል በዓላትን ጠብቆ ማቆየት እና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል። አክለውም ወጣቶች እና በኪነ-ጥበብ ዘርፍ የተሰማሩ ዜጎች እነዚህን እሴቶች በማስቀጠል ረገድ ትልቁን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ክብራለም ደምሴ በበኩላቸው የደብረ ታቦር በዓል ከክረምቱ ድቅድቅ ጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገርን የሚያሳይ፣ የአብሮነት እና የአንድነት ምሳሌ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የበርካታ ባህሎች ባለቤት በመሆኗ እነዚህ ሀብቶች እንዳይበረዙ እና እንዳይረሱ መጠበቅና ማስተዋወቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በዓሉ በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ፕሮግራሞች እና የችቦ ማብራት ሥነ-ሥርዓት በድምቀት ተጠናቋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#DebreTabor #Buhe #AddisAbabaYouth
#EthiopianCulture #AddisAbaba




Source: GetuTemesgen









No comments yet.