#Ethiopia | መጪውን መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ለሚካሄደው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አቶ ኢሳያስ ጅራ ቦሾ ብቸኛ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸው ተገለጸ።
የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴው ቀደም ሲል ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ለጠቅላላ ጉባኤ አባላት ባስተላለፈው ጥሪ መሠረት በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት እስከ ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የዕጩዎች ጥቆማ ሲቀበል ቆይቷል።
ኮሚቴው ነሐሴ 5፣ 11 እና 13 ቀን ባካሄዳቸው ተከታታይ ስብሰባዎች የቀረቡለትን የዕጩዎች ሰነዶች በጥንቃቄ የመረመረና ያጣራ ሲሆን በዚህም መሠረት ለፕሬዝዳንትነት የቀረቡት ብቸኛ ዕጩ አቶ ኢሳያስ ጅራ ቦሾ መሆናቸውን አረጋግጧል።
(EFF)
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.