ከውኃ ውጭ መኖር የማይችለው ታዳጊ አስገራሚና አሳዛኝ ታሪክ!
በህንድ ዌስት ቤንጋል የሚኖረው የ16 ዓመቱ ታዳጊ ኢቅባል ሼክ ላለፉት 5 ዓመታት ሙሉ ህይወቱን ኩሬ ውኃ ውስጥ ለማሳለፍ ተገዷል።
ኢቅባል:-
1. ከውኃ በሚወጣበት ጊዜ በሰውነቱና በቆዳው ላይ ሊቋቋሙት የማይችሉት የሚያቃጥል ከፍተኛ ሕመም ይሰማዋል።
2. ከ11 ዓመቱ ጀምሮ የሚበላው፣ የሚተኛው እና ሙሉ ውሎውን የሚያሳልፈው በኩሬ ውኃ ውስጥ ተዘፍቆ ነው።
3. ቤተሰቦቹ ወደ ተለያዩ ሆስፒታሎች እና ሀገር በቀል ሕክምና ቦታዎች ቢወስዱትም የሕመሙን መንስኤ ማወቅ አልተቻለም ነበር።
ነገር ግን ኢቅባል ውኃ ውስጥ ሆኖ ምግብ ሲመገብ የሚያሳየው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ከተሰራጨ በኋላ፣ ታዋቂው ባለሀብት አናንት አምባኒ የሕክምና ወጪውን ለመሸፈን ቃል ገብቷል።
በአሁኑ ወቅት ኢቅባል በልዩ አውሮፕላን ወደ ሙምባይ ከተማ ተወስዶ በከፍተኛ ሆስፒታል ልዩ የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ይገኛል።
ይህ አስገራሚ ታሪክ የሚያስተምረን ትልቁ እውነት ጤና ከምንም በላይ አስፈላጊ እና ትልቅ ሀብት መሆኑን ነው!
በሰላም መተንፈስ፣ ያለ ሕመም መኖር እና በምቾት በየአካባቢው መንቀሳቀስ መቻል እጅግ ታላቅ ጸጋ በመሆኑ ሁልጊዜ “ተመሰግን” ልንል ይገባል።
ጤናችሁን ጠብቁ፣ ላላችሁ መልካም ጤንነትም ሁልጊዜ ምስጋና አቅርቡ!
@Seledadotio

No comments yet.